Ethiopian for African

Ethiopian for African

Share

INTERNATIONAL MINDS

13/08/2026

የካይሮ አገልጋይ ኢትዮጵያ እና ዜጎቿን ለመሸጥ ግብፅ የሄደበት መረጃ ተጋለጠ

የፖለቲካ ልዩነት ወሰን አለው፤ ሀገርንና ብሔራዊ ጥቅምን አሳልፎ መስጠት ግን የባንዳነት ጥግ ነው! የወጣው የበረራ ትኬት መረጃ እንደሚያስረዳው ይህ ግለሰብ በምስጢር ግብፅ ተገኝቷል። ይህ የመጀመርያ አይደለም፣ ግለሰቡ ለካይሮ እንደሚሰራ የሱዳንን ግጭት ለኢትዮጵያ ሲያላክክ አይተናል፣ ከበቂ በላይ ማረጋገጫ ነው። ለህዝብና ለሀገር ታማኝ ያልሆነ ፖለቲከኛ የህዝብ ወኪል ሊሆን አይችልም። ባንዳነቱን ሁሉም ለመያጋልጥ ይገባል።

13/08/2026

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

13/08/2026

🇪🇹🇪🇹
🏄🏄🏇🏇🏇🏇

Photos from Ethiopian for African's post 13/08/2026

#ዱንጉዛ - የዮ ማስቃላ ሌላኛው ድምቀት!

" ዮ ማስቃላ" የጋሞ ሕዝብ የዘመን መለወጫ፣ የተስፋ፣ የደስታ፣ የአብሮነትና የአዲስ ዘመን መቀበያ በዓል ነው። ይህ በዓል በልዩ ልዩ ባህላዊ ሥርዓቶች፣ በዜማና በውዝዋዜ፣ በባህላዊ ምግቦችና መጠጦች፣ እንዲሁም በተለያዩ የጋሞ ባህላዊ እሴቶች የሚደምቅ ልዩ የምስጋና በዓል ሲሆን፤ ከእነዚህ ድምቀቶች መካከል ግን #ዱንጉዛ ልዩ ስፍራ አለው።

#ዱንጉዛ ልብስ ብቻ አይደለም፤ የጋሞ ማንነት የሚናገርበት ጥበባዊ ቋንቋ ነው። የጋሞ ማህበረሰብ ከጥንት ጀምሮ በሸማ ጥበቡ የፈጠረው፣ በትውልድ ተሻግሮ የመጣው እና የማንነቱን፣ የታሪኩንና የውበት ስሜቱን የሚያንፀባርቀው #ዱንጉዛ፣ በዮ ማስቃላ ወቅት ሲለበስ ደግሞ በዓሉን ከዘመን መለወጫ የምስጋና በዓልነት ወደ ማንነትና ቅርስ ማሳያ መድረክ ይለውጠዋል።

የዱንጉዛ ውበት በሚታየው ቀለምና ቅርጽ ብቻ አይወሰንም። ከጀርባው የተሸመነው የትውልድ ታሪክ፣ የእጅ ጥበብ፣ ትዕግሥት፣ ፈጠራና የማንነት ኩራት አለ። እያንዳንዱ የዱንጉዛ ጥለት እና ቀለም የጋሞን የባህል ውበት በራሱ መንገድ ይመሰክራል። በአንድ በኩል የአባቶችን ቅርስ የሚያስታውስ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ለወጣቱ ትውልድ “ማንነትህን እወቅ፣ ቅርስህን ጠብቅ፣ ወደፊትም አስተላልፍ” የሚል ዝምተኛ መልዕክት ያስተላልፋል።

ዮ ማስቃላ ሲደርስ የጋሞ ሕዝብ በዱንጉዛ ደምቆ በየአደባባዩ ሲታይ፣ የበዓሉ ደስታ የሚገለጸው በሙዚቃና በውዝዋዜ ብቻ አይሆንም፤ የባህል ትዕይንት ጭምር ይሆናል። የአባቶች የሕይወት ተሞክሮ፣ የወጣቱ ጉልበት፣ የሕፃናት ደስታ እና የዱንጉዛ ውበት ተደምረው የጋሞን ሕያው ማንነት ያሳያሉ።

#ዱንጉዛ የዮ ማስቃላ ሌላኛው ድምቀት ነው!! የበዓሉን ውበት የሚያሟላ፣ የጋሞን ማንነት የሚያጎላ፣ የሸማ ጥበብን የሚያስተዋውቅ እና የትውልድ ቅርስን ከዛሬ ጋር የሚያገናኝ የባህል ሀብት ነው።

ዛሬ ዛሬ ዱንጉዛን መልበስ የባህል ውበትን ማሳየት ብቻ ሳይሆን፣ የትናንትን ቅርስ ለነገ ትውልድ ማስረከብ ነው። የጋሞ ሸማ ጥበብ የፈጠረውን ይህን ድንቅ የማንነት መገለጫ በዮ ማስቃላ ማድመቅ ማለት ለባህል ክብር መስጠት፣ ለባህላዊ እውቀት ዋጋ መስጠት እና ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ ሕያው ቅርስ መገንባት ማለት ነው።

12/08/2026

🇪🇹🇪🇹🆗🆗
#ጀግናው

Photos from Ethiopian for African's post 12/08/2026

Ethiopian for African
በአሜሪካ ኦሪገን በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አዲስአበባ ገባ

Photos from Ethiopian for African's post 12/08/2026

💯 ❤️

💯💯💯💯
!!

Ten Unknown Facts About
Founding: Tesla was founded in 2003 by engineers Martin Eberhard and Marc Tarpenning,
not Elon Musk. Musk joined the company as a major investor and became its public face.
Model Naming Quirk: Tesla’s car lineup follows a playful pattern: Model S, 3, X, and Y.
Elon Musk has said it was meant to spell "S3XY," with the number 3 replacing an "E."
Battery Focus: Tesla's breakthrough isn’t just in electric cars but also in battery technology. Tesla has invested heavily in creating
powerful and long-lasting batteries, not only for cars but also for energy storage solutions like Powerwall.
Autopilot and Full Self-Driving: Tesla’s Autopilot is an advanced driver-assistance system, but it’s not fully autonomous. The
company is working on Full Self-Driving (FSD) software, which could eventually enable true autonomous driving.
Gigafactories: Tesla operates massive manufacturing plants known as Gigafactories, located in the U.S., China, and
Germany. These factories are integral to Tesla’s ability to scale production and reduce costs.
SpaceX Connection: Tesla and SpaceX, both run by Elon Musk, share more than just a CEO. The companies collaborate on technology, and
SpaceX’s Falcon Heavy rocket even launched a Tesla Roadster into space as part of a 2018 test flight.
Sustainable Vision: Tesla's mission is to accelerate the world’s transition to sustainable energy.
In addition to electric cars, the company is a leader in solar power and energy storage solutions.
Over-the-Air Updates: Tesla was the first car manufacturer to allow over-the-air software updates, letting owners
download new features and improvements to their cars without visiting a dealership.
AI and Robots:

11/08/2026

Ethiopian for African

Photos from Ethiopian for African's post 11/08/2026

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አስተማማኝ ቁመና

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 05 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አሁን ላይ በሰው ኃይል ብዛት ላይ ብቻ ሳይሆን በጥራት፣ በዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስ እና በላቀ ቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረተ አስተማማኝ አቅም ገንብቷል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሚቀጥሉት ዓመታት አቅሙን ይበልጥ ለማሳደግ ግልጽ ዕቅድ ይዞ እየሠራ ሲሆን፣ ከአራተኛ ትውልድ የውጊያ አውሮፕላኖች ወደ አምስተኛ ትውልድ የማሸጋገር ሂደት ላይ ይገኛል።

በዚህም የሱ-30 እና ጄ-10 የጦር አውሮፕላኖች አቅም፣ የላቁ ሰው-አልባ አውሮፕላኖች እና የኤሌክትሮኒክስ ውጊያ መሣሪያዎች ተቀናጅተው ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው።

የኢትዮጵያ ወታደራዊ ስትራቴጂ ከየብስ ውጊያ ባለፈ የባሕር ኃይል አቅምን እና የውኃ ሀብቶችን ደኅንነት የመጠበቅ ብቃትን በማካተት፣ ሀገራችን በቀጣናው ባሏት ወንዞች እና ግድቦች ላይ ያላትን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብር አቅም ፈጥሯል።

ይህ የሠራዊቷ ብቁ ዝግጅት እና የገቺነት አቅም ብሔራዊ ጥቅሟን ለሚፈታተኑ ታሪካዊ ጠላቶቿ ጠንካራ መልእክት የሚያስተላልፍ እና ሀገራችን ክብሯን በየዋህነት አሳልፋ እንደማትሰጥ የሚያረጋግጥ ነው።

በቀጣናው የሚገኙ ታሪካዊ ጠላቶች የሕዳሴ ግድብን ግንባታ ለማስተጓጎል ያደረጓቸውን ሊነገሩ የማይችሉ የሳቦታጅ ሙከራዎችን በማክሸፍ ረገድ የመከላከያ እና የደኅንነት ተቋማት የማይተካ ሚና ተጫውተዋል።

ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ያለውን የኢኮኖሚ ዕድገት ማሳካት የምትችለው ይህ ጠንካራ የመከላከያ ተቋም ሲኖር ብቻ መሆኑ በግልጽ ታይቷል።

በሀገራዊ ለውጡ መሠረት የመከላከያ ሠራዊቱ ከማንኛውም የፖለቲካ ወገናዊነት ነፃ ሆኖ የሀገራችንን ሉዓላዊነት፣ የሕዝቦቿን ደኅንነት እና ብሔራዊ ጥቅሟን ብቻ የሚጠብቅ ሕዝባዊ ተቋም ሆኖ እየተገነባ ይገኛል።

ሠራዊቱ ከወታደራዊ ግዳጁ ጎን ለጎን በግብርና፣ በመሠረተ-ልማት እና በተለያዩ ሀገራዊ የልማት ሥራዎች ላይ በቀጥታ በመሳተፍ የሀገርን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በማፋጠን ላይ ይገኛል።

ይህ ሁለንተናዊ ዝግጅት፣ ቴክኖሎጂያዊ ሽግግር እና ተቋማዊ የሪፎርም ስራ የኢትዮጵያን ዘላቂ ህልውና የሚያረጋገጥ እና ጦርነትን በማስቀረት ሰላምን የሚያፀና ጽኑ ብሔራዊ ምሰሶ መሆኑን መላው ሕዝባችን በጽኑ ሊገነዘበውና በሠራዊቱ ላይ ያለውን የማይናወጥ እምነት ሊያጎለብት ይገባል። ኢቢሲ

FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

Photos from Ethiopian for African's post 09/08/2026

ሁኔታ የማይበግረው የዓላማ ፅናት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 03 ቀን 2018 ዓ.ም

የአለም ስልጣኔ ቀደምት የነበረችውን ሃገር ጠላቶቿን አስወግዶና ሰላሟን አረጋግጦ ወደ ቀደመ ክብሯ መመለስና ትልቅ እንደነበረች ትልቅ ማድረግ ወታደር ህይወቱን የሚከፍልለት አላማው ነው።

ለዚህም ነው በየጊዜው የሚፈፅመው ጠላትን የመፋለም አድካሚ ግዳጅ ሳይበግረው የውይይት መድረኮችን እየፈጠረ የሰላምን አስፈላጊነት ለህዝብ የሚያስገነዝበውና ሃገር ለመገንባት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ግንባር ቀደም ሆኖ የሚሰለፈው።

ለቀጠናው ሰላም ለህዝብ ነፃነትና ለሃገር እድገት መሰናክል የሆኑ ፀረ-ሰላም ሃይሎችን በጀግንነት ተፋልሞ ድል በመንሳት አደብ ያስገዛል። በሂደቱም መሰናክሎችን በማስወገድ የልማት መንገድ ይጠርጋል ፣ የእድገትን በር ይከፍታል ፣ ዜጎች የሚሹትን የሰላም ዜና ለትውልድ ያበስራል።

ለዘመናት ተከብሮ የኖረውን የሃገር ስምና ታሪክ በከበረ መስዋዕት አስጠብቆ በመዝለቅ የህዝቡን ደህንነት ለማስከበርና የህልውና ጉዳይ የሆነውን ብሔራዊ ጥቅም ለማረጋገጥ በጊዜና በቦታ ሳይወሰን መክፈል የሚጠበቅበትን ዋጋ ሁሉ በጀግንነት ይከፍላል።

የኢትዮጵያ ወታደር በህይወት ዘመኑ ለሃገሩ መስጠት የሚሰስተው አንድም ነገር የለም። ውዲቷን እናት ሃገር ከአንድ እራሱ ሲያስበልጣት ከቃል ባሻገር ምትክ አልባ አንድያ ህይወቱን ያለስስት በመስጠት ነው።

ከጥንትም ጀምሮ የሃገሩን ጠላቶች በጀግንነት ተፋልሞ ድል እየነሳ በየአውደ ግንባሩ ዘመን የማይሽረውና ትውልድ የሚዘክረው አኩሪ ታሪክ ሰርቷል። በሂደቱም የሃገሩን ሉአላዊነት በደሙ አፅንቶ ዳር ድንበሯን በአጥንቱ ፍላፃ በመማገር ለዘመናት በማንም እንዳይደፈር አድርጓል።

እንደተቋም ግዳጁን ሲወጣ የተላበሰው ህብረ ብሄራዊ ገፅታ ከታጠቀው ዘመናዊ መሳሪያ በላይ ጠላቶቹን ድል የሚነሳበት አስተማማኝ ትጥቁ ሆኖለታል። ለዚህም በየዘመናቱ ያሳለፋቸው የአውደ ውጊያ ታሪኮችና ያስመዘገባቸው አንፀባራቂ ድሎች ህያው ምስክር ናቸው።

የትምና መቸም ለተልዕኮው እንቅፋት የሆኑትን ለማስወገድ ሲነሳ ግለቱ የማይቀዘቅዝ ወኔ ታጥቆ ነው ። ለግዳጅ ሲሰማራ የአያት ቅድመ አያቶቹ የጀግንነት ውርስ የሆነውን የአርበኝነት ገድል በተሰለፈበት አውድ ላይ ለመድገም ቃል ገብቶ ነው።

የኢትዮጵያ ወታደር የሚታገልለት አላማ እንደ ሃሰተኞች ትርክት ከየትኛውም የፖለቲካ ተቀፅላ የሚቀዳ ሳይሆን ከህዝባዊ ወገንተኝነቱና ካለው ፅኑ የሃገር ፍቅር ስሜት የሚመነጭ ነው።

አሁን ላይ ወታደሩ በወታደራዊ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ከአለም ጋር ተወዳዳሪ ሆኖ ወደ ስልጣኔ እያመራና ዘመንን እየዋጀ ያለበት ጊዜና ወቅት ላይ ነው። ወትሮም ቢሆን ሰራዊቱ በሃገሩ ከመጡበት ከሽንፈት ሞትን ይመርጣል የአላማ ፅናቱን ሁኔታ አይበግረውም። ለሀገሩ ሠላም፣ ለሠንደቅ ዓላማው ክብር፣ ለብሄራዊ ጥቅም መከበርና ዛሬም በተጠንቀቅ የቆመው ሠራዊት ምንጊዜም ለሀገሩ ሲል ህይወቱን አሳልፎ ለመሥጠት አይሰስትምና ክብር ለወታደሩ ይሁን።
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa
GOOD