Etcare
An official page of Etcare, Etcare is a company that produces and sell beauty care products
10/08/2026
ቀንዎን በፈገግታ ከአልቤንት ጋር ይጀምሩ!
Etcare
08/08/2026
አዲስ የስልጠና መድረክ በኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት
ከፊታችን ሰኞ ነሀሴ 04 ጀምሮ በኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት አዳራሽ
በኢቲኬር ኤሊት አምባሳደሮች እና ማስተር አሰልጣኞች ተመስገን ሀይሉ እና ኢንጂነር ታጠቅ ጌታቸው ጋር
ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ
መግቢያ፡ የሲስተም ማኑዋኑን ይዞ መገኘት ብቻ
ከሰኞ ጀምሮ በሚኖሩ የስልጠና መድረኮች የቀጥተኛ ሽያጭ ጉዞዎን በሲስተም እና በስር አት ለመገንባት የሚያስችልዎትን ስልጠናዎች ያግኙ።
ሰኞ እንገናኝ።
Etcare
የቆዳዎን እንክብካቤ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግሩ!
Etcare ለላቀ ውበት!
07/08/2026
ቅዳሜ ከሰአት በኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት አዳራሽ
የታቀደ ታቅዶም የተፈጸመ ተፈጽሞ ስኬት ላይ ያደረሰን የቀጥተኛ ሽያጭ መንገድ ከኗሪው አንደበት በጥሩ የመድረክ አቅም ልንቀስም ቀጠሮ ይዘናል።
ነገ ቅዳሜ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ቀጠሮቆ በኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት ከሆነ የቀጥተኛ ሽያጭ ልምድን ከህይወት መርህዎች ጋር ተጣምረው ወደ እናንተ ሊያደርስ የኢቲኬር ማስተር አሰልጣኝ እና ኤሊት አምባሳደር ተመስገን ሀይሉ ይጠብቅዎታል።
በመድረኩ የኢቲኬርን አሰራር እና አከፋፈል ከምርት እና ቢዝነስ ገለጻው አጣቅሶ በኢቲኬር ሊድ ቲም አባል ኤፍሬም ተፈራ ገለጻ ተዘጋጅቷል።
መድረኩን የኢቲኬር ፕሮፌሽናል አሰልጣኙ ዮሀንስ ሲሳይ ይመራዋል።
ነገ ቅዳሜ ነሀሴ 02
ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ
በኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት አዳራሽ
መግቢያ በነጻ
Etcare
04/08/2026
እንኳን ደስ አላችሁ
የሌላ ከፍታ የሌላ ብስራት የሌላ ስኬት ጅማሮ!
በጉጉት የሚጠበቀው የኢቲኬርን ቀጣይ የዌልነስ ምርቶች መንገድ ሀ ብሎ የሚጀመርበት የ ስፓይሩሊና ፕሮጀክት ከ ማምረቻ ስፍራ እና የ ኮንስትራክሽን ስራዎች አልፎ ዛሬ ላይ የማምረቻ የላብራቶሪ መሳሪያዎች ባለቤትነትን በይፋ አብስሯል።
የኢቲኬር ስፓይሩሊና ምርቶችን ለማምረት እና ወደ መሬት ለማውረድ ወሳኝ ምእራፍ እንደሆነ የሚነገርለት የ ላቦራቶሪ መሳሪያዎች ግዢ በአውሮፓ ከሚገኘው እና በዘርፉ የበርካታ አመታት ልምድ ካለው አምራች ድርጅት ግዢ በመፈጸም ዛሬ በሞጆ ደረቅ ወደብ የንብረት ርክክብ ተደርጓል።
የኢቲኬር የማኔጅመንት አባላት እና የፕሮጀክቱ መሪ ተመራማሪ በስፍራው በመገኘት እነዚህን ንብረቶች ርክክብ አድርገዋል።
ይህ ምእራፍ የስፓይሩሊና ፕሮጀክታችንን ብስራት ይበልጥ ያቀረበ ይበልጥ ወደ እውነታ ያመጣ የኢቲኬርን በእቅዶቹ ላይ ያለውን ቁርጠኝነት በጉልህ የሚያሳይ ሲሆን እነዚህ የላቦራቶሪ ምርቶች በቀጣዮቹ ቀናት ከሞጆ ደረቅ ወደብ ተነስተው ወደ ቡልቡላ ኢንተግሬትድ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ በመጓጓዝ በኢቲኬር ስፓይሩሊና ፕሮጀክት ፋርም ላይ የሚደርሱ ይሆናል።
04/08/2026
https://youtu.be/r2f6TSmmdmE?si=bxx2M4NYzTyXy7xP
ለብርዱ መፍትሄ አግኝቻለው ! የኢቲኬርን ምርቶች ከተጠቀሙት አንደበት ሲዳሰስhttps://www.tiktok.com... https://www...
02/08/2026
የእውቅና መርሀግብር በባህርዳር ኢቲኬር
ኢቲኬር ባህርዳር አሰልጣኞቹን በአደባባይ እውቅና ሰጥቷል።
የኢቲኬር ባህርዳር ቅርንጫፍ ዛሬ በሳፋሪ ሞል ባዘጋጀው የእውቅና መሰናዶ በድምቀት ተከናውኗል።
በምርት እና ቢዝነስ ገለጻ የጀመረው መሰናዶ በድርጅታችን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሳሙኤል ተክለየሱስ የድርጅቱን ጉዞ እና የወደፊት እቅዶች ላይ ትኩረቱን ያደረገ መግለጫ በመሰናዶው ለተገኙ እንግዶች የተብራራ ሲሆን በመሰናዶው ማብቂያ ሲጠበቅ የነበረው ቀጣዮቹ የኢቲኬር ኤክስፐርት አሰልጣኞችን እውቅና የመስጠት ዝግጅት በድርጅታችን ምክትል ስራ አስኪያጅ መሪነት ተከናውኗል።
በዚህም መሰረት ከኢቲኬር ባህርዳር ቅርንጫፍ ሪጅናል ዳይሬክተር መለሰ አያሌው እና ከ ደብረማርቆስ ቅርንጫፍ ማናጀር ይልቃል አንዱ አለም የ ኤክስፐርት አሰልጣኝነት እውቅናን በይፋ ተቀብለዋል።
ሌላው በመድረኩ የማናጀርነት ደረጃን ላሳካው አስራት ማረፊያው የእውቅና መሰናዶ ተከናውኗል።
ለእንግዶች በተበረከተ የስጦታ መሰናዶ እና ምስጋና ማብቂያውን ያደረገው ይህ የኢቲኬር ባህርዳር መሰናዶ የሰሩን በአደባባይ ያከበረ ለመስራት በእቅድ ያሉትን ከእቅድ ወደ ተግባር እንዲገቡ መንገድ የከፈተ ሆኖ አልፏል።
02/08/2026
በኢቲኬር ባህርዳር ደማቅ የስልጠና መድረክ እየተከናወነ ይገኛል።
ዛሬ ሀምሌ 26 በኢቲኬር ባህርዳር የተሰናዳው የመሪነት ስልጠና በኢቲኬር ምክትል ስራ አስኪያጅ ሳሙኤል ተክለየሱስ ተከናውኗል።
በሳፋሪ ሞል በተሰናዳው በዚህ መሰናዶ ላይ የጠዋቱን ክፍለጊዜ ለታደሙ ኢቲኬሪያንስ የመሪነት ጽንሰ ሀሳብ ላይ መሰረት ያደረገ የስልጠና መድረክ ተሰጥቷል።
ለመማር ዝግጁ የሆኑ የኢቲኬር ባህርዳር ኢቲኬሪያንስ ይህንን ስልጠና በንቃት የተከታተሉ ሲሆን በስልጠናው በቀጥተኛ ሽያጭ ላይ መሰረት ያደረጉና አለም አቀፍ የመሪነት ህግ እና ቁልፎችን ያማከሉ የስልጠና ሀሳቦች የተነሱበት መድረክ ሆኖ ተከናውኗል።
31/07/2026
ቅዳሜን በደሴ
ታላላቆቹ የኢቲኬር አሰልጣኞች ማስተር አሰልጣኞቹ ኤሊት አምባሳደር ተመስገን ሀይሉ እና ኤሊት አምባሳደር ኢንጂነር ታጠቅ ጌታቸው በደሴ አልማ አዳራሽ በደሴ ከሚገኙ ኢቲኬሪያንስ ጋር በህይወት ክህሎት ስልጠና ይገናኛሉ።
ነገ ቅዳሜ ሀምሌ 25
ከቀኑ 9 ሰአት ጀምሮ
በደሴ አልማ አዳራሽ እንገናኝ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Https://maps. App. Goo. Gl/9awY8x3TpHfJixMi 9
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 07:00 |
| Tuesday | 08:00 - 13:00 |
| Wednesday | 08:00 - 13:00 |
| Friday | 08:00 - 13:00 |
| Sunday | 08:00 - 13:00 |