Meznagnia Media

Meznagnia Media

Share

Celebrating 10 Years.

Salem Media (ሳሌም) is a digital and print publication that focuses on lifestyle, news, arts, and entertainment in the Ethiopian, Eritrean, and African communities in the United States.

01/08/2026

የኢትዮጵያ ታዳጊ እግር ኳስ ተጫዋቾች ሙሉ በሙሉ በስዊድን መሰወራቸው ተገለፀ

በስዊድን ጎተንበርግ ከተማ በተካሄደው የ2026 የጎቲያ ካፕ (Gothia Cup) የወጣቶች አለም አቀፍእግር ኳስ ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበረውና የኢትዮጵያ ወጣቶች ቡድን ልዑክ አባላት የሆኑ 20 ያህል ግለሰቦች መጥፋታቸው ተገለፀ።

የስዊድን ፖሊስ ባለሥልጣንናት እንደገለፁት፣ የጠፉት ግለሰቦች ዕድሜያቸው ከ14 እስከ 17 ዓመት የሆኑ ታዳጊ ወንዶች እና ቢያንስ አንድ አዋቂየቡድኑ መሪ መሆናቸው ተገልጿል ።

የቡድኑ መሰወር የታወቀው የውድድሩ አስተባባሪዎችበዝግጅቱ ማጠቃለያ ቀን የቡድኑ አባላት ካረፉበት ማረፊያ ክፍሎች ሳያሳውቁ ሙሉ በሙሉ ለቆ በመውጣት መሰወራቸውን ባስተዋሉበት ወቅት ነው።

የዝግጅቱ አዘጋጆች የኢትዮጵያተሳታፊ ቡድን አባላት ሙሉ ለሙሉ መሰወራቸውን ለፖሊስ አስታውቀዋል።ሕግ አስከባሪ አካላት ባደረጉት ማጣሪያም ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የተቆረጠለትን የጉዞ በረራ እንዳልተጠቀመ አረጋግጠዋል።

በክስተቱ ዙሪያ የወንጀል ወይም የሰዎች ዝውውር (Human Trafficking) ምልክት አለመገኘቱን የገለጸው ፖሊስ፣ ጉዳዩን “በራስ ፈቃድ መጥፋት” በሚል መዝግቦታል።

ይህም ታዳጊዎቹ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፈተና በመሸሽ በስዊድን ጥገኝነት (Asylum) የመጠየቅ ሐሳብ ሳይኖራቸው እንዳልቀረ ግምቶችን አስከትሏል።

በአሁኑ ወቅት ፖሊስ ከስዊድን የስደተኞች ኤጀንሲ እና ከድንበር ጥበቃ ፖሊስ ጋር በመተባበር ግለሰቦቹ ያሉበትን ቦታ ለመለየት የተጠናከረ ክትትል እያደረገ ይገኛል።

የጎቲያ ካፕ አዘጋጆች በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያው ክለብ ተወካይ ታዳጊዎቹ ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑንና በኢትዮጵያ ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ማድረጋቸውን እንዳረጋገጠላቸው ገልጸዋል።

በዓለማችን በትልቅነቱና በተደራሽነቱ ቀዳሚ የሆነው የጎቲያ ካፕ (Gothia Cup) የወጣቶች እግር ኳስ ውድድር ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተውጣጡ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ታዳጊዎችን በማሳተፍ በስዊድን ጎተንበርግ ከተማ በደመቀ ሁኔታ በየዓመቱ የሚካሔድ የታዳጊዎችና ወጣቶች የእግር ኳስ ውድድር ነው።

እ.ኤ.አ. በ1975 በጎተንበርግ እግር ኳስ ክለቦች የተመሠረተውና ዕድሜያቸው ከ11 እስከ 18 ዓመት ለሆኑ ወንዶችና ሴቶች ክፍት የሆነው ይህ ውድድር፣ ዘንድሮም ከ80 በላይ ከሚሆኑ ሀገራት የመጡ ከ40,000 በላይ ታዳጊዎችን ማሳተፍ መቻሉ ታውቋል።

“የወጣቶች ዓለም ዋንጫ” (World Youth Cup) በሚል መሪ ቃል የሚታወቀው ይህ ታላቅ መድረክ፣ ከስፖርታዊ ውድድርነቱ ባሻገር የተለያየ ባህል፣ ሃይማኖትና ዘር ያላቸው ታዳጊዎች የሚገናኙበትና አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበት ልዩ መድረክ ሆኖ አገልግሏል። ውድድሩ በታሪኩ እንደ አንድሪያ ፒርሎ፣ ዝላታን ኢብራሂሞቪች እና አላን ሽረር ያሉ ዝነኛ የዓለም እግር ኳስ ኮከቦችን በታዳጊነታቸው ያሳተፈና ያፈራ መሆኑም በዘገባው ተመልክቷል።

Meznagnia / መዝናኛ

31/07/2026

በፖቶማክ ወንዝ ውስጥ ጠፍቶ የነበረው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ወጣት አስክሬን ተገኘ

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በታዋቂው ግሬት ፎልስ (Great Falls) ደቡባዊ አቅጣጫ በፖቶማክ ወንዝ ውስጥ ዋና ላይ እያለ ጠፍቶ የነበረው የ25 ዓመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ኢሳን ናስር (Isan Nassir) አስክሬን በሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ ግዛት ወሰን ድንበር ላይ መገኘቱን የነፍስ አድን ቡድኖች አስታውቀዋል።

ወጣቱ በዚህ በጋ ወቅት ብቻ በዚሁ አስፈሪ የወንዙ አካባቢ ህይወቱ ያለፈ ሶስተኛው ሰው ሆኗል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የእሳት አደጋ እና ነፍስ አድን አገልግሎት (Montgomery County Fire and Rescue) እንደገለጸው፣ የፈጣን ውሃ ነፍስ አድን ቡድኑ የሟቹን አስክሬን ሐሙስ ረፋድ 11:30am ሰዓት ላይ አግኝቶታል።

ቡድኑ አስክሬኑን ሊያገኝ የቻለው ሶናር (sonar) እና የውሃ ውስጥ ካሜራ ምስሎችን በመጠቀም ወጣቱ መጨረሻ ጊዜ ከታየበት ስፍራ ብዙም ሳይርቅ ነው።

ባለፈው ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ወጣቱ በውሃው ውስጥ እንደሰመጠ ጥቆማ የደረሳቸው የዩኤስ ፓርክ ፖሊስ (US Park Police) አባላት ወዲያውኑ ወደ ስፍራው ደርሰው አሰሳ ቢያደርጉም ሊያገኙት ሳይችሉ ቀርተዋል፣ እርሱ የጠፋበት አካባቢ ወንዙ እስከ 50 ጫማ (15 ሜትር) ጥልቀት ሊኖረው እንደሚችል ባለስልጣናት ገልጸዋል።

በተያያዘ መረጃ፣ በዚህ በጋ ወቅት በተመሳሳይ የወንዙ አካባቢ በተከሰቱ ሁለት የተለያዩ አደጋዎች የሌሎች ሁለት ወጣቶች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

የፓርኩ ባለስልጣናት በፖቶማክ ወንዝ ውስጥ መዋኘት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን በድጋሚ እያሳሰቡ፣ በላይኛው ገጽ ላይ የተረጋጋ የሚመስለው ውሃ ከውስጥ እጅግ አደገኛ እና ገዳይ የሆኑ የአየር እና የውሃ ሞገዶች (currents) ሊኖሩት እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

31/07/2026

የአማዞን ሶፍትዌር መሃንዲስ በሌክ ታሆ (Lake Tahoe) ሃይቅ ውስጥ ሰምጦ ህይወቱ ማለፉ ተገለጠ

በቴክሳስ ግዛት ኦስቲን ከተማ የአማዞን ኩባንያ የሶፍትዌር መሃንዲስ የነበረው የ32 ዓመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ያደሳ አጋ፣ ሰኞ ምሽት በኔቫዳ ግዛት በሚገኘው ዝነኛው ሌክ ታሆ (Lake Tahoe) ሃይቅ ውስጥ እየዋኘ እያለ በደረሰበት ድንገተኛ አደጋ ህይወቱ ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

የዋሾ ካውንቲ (Washoe County) የህክምና ምርመራ ቢሮ የሟቹን ማንነት ያረጋገጠ ሲሆን፣ ያደሳ በኦስቲን ከተማ ለታዋቂው የቴክኖሎጂ ግዙፍ ኩባንያ አማዞን በሶፍትዌር መሃንዲስነት ይሰራ እንደነበር የሊንክድኢን (LinkedIn) ማህበራዊ ገጹ ያሳያል።

የዋሾ ካውንቲ ሸሪፍ ቢሮ እንደገለጸው፣ የነፍስ አድን ጥሪው የደረሳቸው ሰኞ ምሽት 8:00 PMሰዓት አካባቢ በሰንድ ሃርበር (Sand Harbor) የመዝናኛ ስፍራ የጀልባ ማቆሚያ አቅራቢያ ነበር።

መርማሪዎች እንዳረጋገጡት ያደሳ ጀንበር ልትጠልቅ አካባቢ በሃይቁ ዳርቻ አካባቢ እየዋኘ በነበረበት ወቅት፣ በድንገት በውሃው ውስጥ ሰምጦ ሊገባችሏል። በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ከውሃው ዉስጥ አውጥተው ህይወት አድን የመጀመሪያ እርዳታ ቢያደርጉለትም ሊያድኑት አልቻሉም።

የጸጥታ አካላት እና የህክምና ባለሞያዎች በስፍራው ከደረሱ በኋላ እሱን ለማዳን ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ወዲያውኑ የልብና የሳምባ መነቃቂያ (CPR) የነፍስ አድን እርዳታ ቢያደርጉለትም ህይወቱን ማዳን አልተቻለም።

የፖሊስ ባለስልጣናት በአሁኑ ወቅት ጉዳዩን እንደ ድንገተኛ የውሃ ውስጥ መስጠም አደጋ (accidental drowning) እየተመለከቱት ቢሆንም፣ ይፋዊ የሞት መንስኤውን በትክክል ለማወቅ አሁንም ንቁ እና ሰፊ ምርመራ እያደረጉ መሆኑን አስታውቀዋል።

የጎ ፈንድ ሚ ሊንኩን ኮመንት ላይ አስቀምጠናል።

Meznagnia / መዝናኛ

30/07/2026

ታሪካዊ ክስተት፦
ኪኪ ራሞስ ለአርጀንቲና ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን አደረገ

ወጣቱ የፊት መስመር ተጫዋች ኪኪ ራሞስ ለአርጀንቲና ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን በማድረግ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ አስመዝግቧል።

ተጫዋቹ በማንኛውም የዕድሜ እርከን የአርጀንቲናን ብሔራዊ ቡድን የወከለ የመጀመሪያው ትውልደ-ሄቲ ተጫዋች መሆን ችሏል።

በፈረንጆቹ 2009 በሄቲ የተወለደው ኪኪ ራሞስ፣ ከ300,000 በላይ የሰዎችን ሕይወት የቀጠፈውን አስከፊውን የ2010 የሄቲ የመሬት መንቀጥቀጥ በተአምር የተረፈ ጠንካራ ስፖርተኛ ነው። ከክስተቱ በኋላ ገና የ8 ወር ሕፃን እያለ በአርጀንቲናዊ ቤተሰብ በማደጎ ልጅነት ተቀብለውት ወደ ደቡብ አሜሪካ አቅንቷል።

በአሁኑ ወቅት በታዋቂው ለቬሌዝ ሳርስፊልድ በመጫወት ላይ የሚገኘው ይህ ተስፈኛ ኮከብ፣ ዝነኛውን የደቡብ አሜሪካ ሀያል ሀገር ማሊያ በመልበስ በይፋ ታሪክ ሰርቷል።

29/07/2026

ያን ዲዮማንዴ የሪያል ማድሪድን ማሊያ ለበሰ፤ በስኬቱ ጀርባ ያለው ልብ ሰባሪ ታሪክ

ያን ዲዮማንዴ የዓለማችን ግዙፉን ክለብ ሪያል ማድሪድን በይፋ መቀላቀሉን ተከትሎ፣ የእግር ኳሱ ዓለም ስለ ተጫዋቹ ድንቅ ብቃት እያወራ ይገኛል። ሆኖም ከዚህ ታላቅ ስኬት በስተጀርባ ተጫዋቹን ለዛሬው ክብር ያበቃችው፣ ነገር ግን ስኬቱን ለማየት ያልታደለችው እህቱ ሮክሳን ልብ ሰባሪ ታሪክ አለ።ዲዮማንዴ ዛሬ ላይ ለመድረስ እጅግ አስቸጋሪ የፈተና ቀናትን አሳልፏል።

ቀደም ሲል በበርንማውዝ፣ ቼልሲ፣ ሬንጀርስ እና ክሪስታል ፓላስ የሙከራ ጊዜያትን ቢያሳልፍም «አትመጥንም» በሚል ውድቅ ተደርጎ ተሸኝቷል። በወቅቱ በክሪስታል ፓላስ ቤት የነበሩት ድንቅ ተጫዋቾች ኤቤሬቺ ኤዜ እና ማይክል ኦሊሴ ከልምምድ በኋላ ብቃቱን አድንቀው ቢያበረታቱትም፣ የክለቦቹ በር ግን ተዘግቶበት ነበር።በእነዚያ ዓለም ፊቷን ባዞረችበት የጭንቅ ቀናት ውስጥ፣ በአጠገቡ በመሆን ብቸኛ የብርታት ምንጭ የሆነችው እህቱ ሮክሳን ነበረች።

ገና እውነተኛ የእግር ኳስ ጫማ እንኳ ሳይኖረው «አንተ ቀጣዩ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ነህ፤ ወንድሜ በዓለም ላይ ምርጡ ተጫዋች ይሆናል» እያለች እምነቷን ትመሰክርለት ነበር። በቴሌቪዥን የኪሊያን ምባፔን ጨዋታ በሚመለከቱበት ወቅትም «ምባፔ ጎበዝ ነው... ግን የእኔ ወንድም ይበልጠዋል» በማለት የተስፋ ስንቅ ትሆነው እንደነበር ይታወሳል። ዛሬ ሮክሳን የተናገረችው ትንቢት እውን ሆኖ ዲዮማንዴ የሪያል ማድሪድን ማሊያ ለብሷል።

በሜዳ ላይም ከፈረንሳዩ ኮከብ ኪሊያን ምባፔ ጋር ማሊያ ተቀያይሯል። ነገር ግን ይህንን ታላቅ ድል አብራው የምታከብረው እህቱ በህይወት የለችም።ዲዮማንዴ እህቱን በማስታወስ ባስተላለፈው ልብ የሚነካ መልዕክት፦ «ሮክሳን... እኔ ትልልቅ ቪላዎችን ወይም ውድ መኪኖችን አልተመኘሁም። የፈለግኩት አንድ ነገር ብቻ ነበር—አንቺ ስለ እኔ የተናገርሽው እውነት መሆኑን ለዚህ ጨካኝ ዓለም ማሳየት! ዛሬ ሜዳው ለእኔ ኳስ መጫወቻ ብቻ አይደለም፤ በፀጥታ ከአንቺ ጋር የምነጋገርበት እና ድምፅሽን የምሰማበት መጠጊያዬ ነው» ብሏል።

ዲዮማንዴ ስኬቱ ሙሉ የሚሆነው እህቱ በህይወት ኖራ እጁን ስትይዘው የነበረ ቢሆንም፣ እስከ መጨረሻው እስትንፋሱ ድረስ እሷ ትክክል እንደነበረች ለዓለም ለማረጋገጥ ቃል ገብቷል።

በኤፕሪል 2025 ዓ.ም. የያን ዲዮማንዴ የ15 ዓመት እህት ሮክሳን በአንድ ድግስ ላይ ትጠጣው የነበረዉ መጠጥ ሆን ተብሎ እርሷን ለመጉዳት ታስቦ የተመረዘ ስለነበረ፣ ከጠጣቸው በኋላ ወዲያውኑ ራሷን ልትስት ችላለች፣ ከሰዓታት ቆይታ በኋላም ህይወቷ ሊያልፍ ችሏል።

ዲዮማንዴ ስለ ድርጊቱ ትክክለኛ ሁኔታ ወይም መጠጡ ውስጥ መርዝ የተበረዘበትን ምክንያት (አላማ) በተመለከተ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ቁርጥ ያለ መልስ እንዳላገኘ አካፍሏል።

28/07/2026

የእግር ኳስ ኮከቡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ጆርጂና ሮድሪጌዝ በሴፕቴምበር 2026 ጋብቻቸውን በይፋ እንደሚፈጽሙ ተገለጠ።

ታዋቂው የፖርቹጋል እግር ኳስ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና የረጅም ጊዜ ፍቅረኛው ጆርጂና ሮድሪጌዝ በፈረንጆቹ መስከረም (ሴፕቴምበር) 2026 የጋብቻ ስነ-ስርዓታቸውን እንደሚፈጽሙ የፖርቹጋል መገናኛ ብዙሃንን ጠቅሶ የወጡ ዘገባዎች አመልክተዋል።

ጥንዶቹ ለአስር ዓመታት ያህል በፈጠሩት የፍቅር ግንኙነት ቆይታ በኋላ በነሐሴ (ኦገስት) 2025 ዓ.ም ይፋዊ የእጮኝነት ጥያቄ መለዋወጣቸው ይታወሳል።

መጀመሪያ ላይ በሐምሌ (ጁላይ) ወር መጨረሻ ላይ ሊከናወን ታቅዶ የነበረው የሰርግ ስነ-ስርዓት፤ የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ከ2026 የዓለም ዋንጫ መሰናበቱን ተከትሎ ወደ መስከረም (ሴፕቴምበር) 2026 እንዲዛወር ተደርጓል።

ይህ በጉጉት የሚጠበቀው ደማቅ ሰርግ በሮናልዶ የትውልድ መንደር ማዴራ ደሴት በሚገኘው ታሪካዊው የፉንቻል ካቴድራል (Funchal Cathedral) ውስጥ እንደሚከናወን ይጠበቃል።

Daniel Gebremariam

28/07/2026

አሜሪካዊቷ ቲክቶከር ባለቤቷ ህፃናትን አስገድዶ ደፋሪ መሆኑን በቀጥታ ቲክቶክ ላይ ከተናገረች ከሁለት ሳምንት በኋላ መገደሏ ተሰማ

በማህበራዊ ሚዲያ ታዋቂ (influencer) የነበረችው ሳራ ጊልሰን፣ በቲክቶክ ገጿ ላይ ባለቤቷን “ህጻናትን አስገድዶ የሚደፍር (pedophile)” ነው ስትል ከከሰሰችው ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ፣ በተቀየማት ባለቤቷ መገደሏን ፖሊስ እና የፍርድ ቤት መዝገቦች አስታውቀዋል።

የ43 ዓመቷ ሳራ ጊልሰን በአሜሪካ ኦክላሆማ ውስጥ በባለቤቷ ጀረሚያ ደፊ (በማህበራዊ ሚዲያ ስሙ ሾን ደፊ በሚባለው) ሐሙስ ዕለት በጥይት ተመትታ መሞቷን የኦዋሶ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

ከግድያው አንድ ወር ቀደም ብሎ፣ ፖሊስ ባለቤቷ ህጻን ልጅ አስገድዶ በመድፈር ወንጀል መጠርጠሩን ከነገራት በኋላ፣ ሳራ የአስቸኳይ ጊዜ የጥበቃ ትዕዛዝ አውጥታ ነበር።ሳራ የቲክቶክ ገጿ ላይ ባጋራችው ቪዲዮ፥ “ኔትፍሊክስ (Netflix) በቅርቡ ስለሚፈታው እና ህጻናትን አስገድዶ መድፈር ወንጀለኛ ስለሆነው ባለቤቴ ዘጋቢ ፊልም ሲያወጣ ለመመልከት እየተዘጋጀሁ ነው” በማለት በወቅቱ በሰፊው ይሰራጭ የነበረውን የኔትፍሊክስ የትሬንድ ቪዲዮ ተጠቅማ ተናግራ ነበር።

ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ጀረሚያ ደፊ የሴቶች የቅርጫት ኳስ ቡድን አሰልጣኝ የነበረ ሲሆን፣ በአንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በተደረገ ዝግጅት ላይ አንዲትን ህጻን ልጅ አግባብ ባልሆነ መልኩ መደባበሱ በፖሊስ ተመዝግቦ ነበር።

ሳራ የባለቤቷን አፀያፊ ድርጊት ለህዝብ በይፋ በማህበራዊ ሚዲያ ከገለፀች በኋላ ፣ ባለቤቷ በድርጊቷ ክፉኛ ተበሳጭቶ ከአካባቢው ለሁለት ሳምንታት ተሰውሮ የነበረ ሲሆን፣ ባሳለፍነው ሳምንት ሐሙስ ግን ሳይታሰብ ወደ መኖሪያ ቤቱ በመመለስ ሳራን ጭንቅላቷ ላይ በመተኮስ ከገድላት በኋላ የራሱን ህይወትም ሊያጠፉ መቻሉን ፖሊስ አክሎ ገልጿል።

ፖሊስ ጉዳዩን እያጣራ ቢሆንም፣ ክስተቱ ባለቤቷ ሳራን ገድሎ እራሱንም ያጠፋበት (murder-suicide) እንደሆነ ገልጿል። ሳራ ጊልሰን የአንድ ወንድ እና የአንድ ሴት ልጅ እናት ነበረች።

Daniel Gebremariam

26/07/2026

ሻኪራ በኡጋንዳውያን ህፃናት ተሰጥኦ በመደመም ድጋፍ እንደምታደርግ ቃል ገባች

ታዋቂዋ የሙዚቃ ኮከብ ሻኪራ በፊፋ የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ መድረክ ላይ አብረዋት የደነሱትን የኡጋንዳ ህፃናት (Ghetto Kids) ስሜታዊ በሆነ እምባ ተሰናበተቻቸው።

ሻኪራ በታዳጊዎቹ ልዩ ተሰጥኦ መደመሟን ገልጻ፣ በቀጣይ ድጋፍ እንደምታደርግላቸው ቃል ገብታለች።የግራሚ ሽልማት አሸናፊዋ ድምፃዊት እነዚህ ካልተመቻቸ የህይወት ታሪክ ውስጥ የወጡ ህፃናት ባላቸው ተሰጥኦ እና በሚያሳዩት ደስታ ዓለምን ማነሳሳታቸውን አድንቃለች።

ይህንኑ መድረክ በመጠቀምም መንግስታት፣ የግል ድርጅቶች እና ባለሙያዎች በተረሱ ሁኔታዎች ውስጥ ለሚኖሩ ህፃናት እኩል እድል እንዲፈጥሩ እና ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርባለች።

ሻኪራ ከትዕይንቱ በኋላ ህፃናቱን እያቀፈች ስታለቅስ የሚያሳይ ቪዲዮ በኢንስታግራም ገጿ ላይ ያጋራች ሲሆን፣ በፅሁፏም፦ “የኡጋንዳው Ghetto Kids ተላላፊ የሆነ ደስታ እና ፍቅር ይዘውልን መጥተዋል። እንደነሱ ያሉ በርካታ ተረስተው የሚኖሩ ነገር ግን ትልቅ አቅም ያላቸውና እድል ብቻ የሚጠብቁ ህፃናት እንዳሉ በችሎታቸው አስታውሰውናል” ስትል መልዕክቷን አስተላልፋለች።

Daniel Gebremariam

25/07/2026

የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ኮከብ ዴቪድ ቤካም በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ላይ ተጫውቶ ጎል ማስቆጠር ሳያስፈልገው የውድድሩ ከፍተኛ የገቢ ተጠቃሚ መሆኑ ተገለጠ።

የገበያ ተንታኞች ባወጡት መረጃ መሠረት፣ የ51 ዓመቱ የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋች እንደ ሌይስ (Lay’s)፣ አዲዳስ (Adidas)፣ ማክዶናልድስ (McDonald’s)፣ ባንክ ኦፍ አሜሪካ (Bank of America) እና ስቴላ አርቶይስ (Stella Artois) ካሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ባደረጋቸው የማስታወቂያ ስምምነቶች ከ24 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት ችሏል።

በሌላ በኩል ታዋቂዋ ድምፃዊት ሻኪራ በውድድሩ ሁነቶች ላይ ካደረገችው ተሳትፎ እና ከማስታወቂያ አጋርነቶቿ 20.5 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቷ ተመልክቷል።

በአሁኑ ወቅት ቤካም የመጀመሪያው ብሪታንያዊ ቢሊየነር ስፖርተኛ መሆን የቻለ ሲሆን፣ ይህም የስፖርት ባለሙያዎች የእግር ኳስ ተጫዋቾች ካላቸው ሜዳ ላይ ስኬት ባሻገር የግል ስማቸውን (Personal Brand) ለገበያ በማቅረብ ረገድ ያላቸውን ውጤታማነት በግልጽ ያሳየ ሁነት ሆኗል።
⚽💼

Daniel Gebremariam

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


50 S Pickett Street
Addis Ababa
22304

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00