Ethio culture business center

Ethio culture business center

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio culture business center, Health/Beauty, Street, Gelemso.

23/10/2021

ህወሓት የመጨረሻውን እድሉን እየሞከረ ነው። ከኋላ ምንም ዓይነት ደጀን ሳያስቀር ሁሉንም ሃይሉን ጠራርጎ አሰልፏል። አንካሳ፣ ቆራጣ፣ የአካል ጉዳተኛ፣ ጡረተኛ፣ ማየትና መስማት የተሳነው፣ የጎዳና ተዳዳሪ፣ የእኔ ብጤ፣ በዚህኛው ዙር የቀረ የለም። ከህወሀት ኮማንድ ፖስት የተሰማውም ይህ ዙር ጦርነት የመጨረሻው መሆኑን ነው። ማሸነፍ አልያም መሞት። እነታደሰ ወረደ ከሁለት ሳምንት በፊት ጦርነቱን ለመጀመር የሚያስችለውን ምክክር ሲያደርጉ ወይ እንጠፋለን አልያም እናሸንፋለን፣ ለዚህም ያለንን ሁሉ ይዘን እንዋጋለን የሚል ውሳኔ ማስተላለፋቸው ታውቋል። ጻድቃን ገ/ትንሳይ ባለፈው ሳምንት ለውጭ ሚዲያ ሲናገር ጦርነቱ ከሁለት ሳምንት በላይ ሳይዘልቅ ለማጠናቀቅ ተዘጋጅተናል ማለቱ ይህ ዙር የፍጻሜ እንደሚሆን የሚያመላክት ነው። የቁም ኑዛዜ ይሆን?

በእርግጥም ህወሓት ከስሩ ተነቅሎ አሰስ ገሰሱን ጭኖ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎና አፋር ተሰብስቧል። ወገኑ ካልሆነው ህዝብ ከሚኖርበት ድንበር ዘልቆ ገብቷል። ከሰኔ ወር ወዲህ ህዝባዊ ማዕበል እንዲሆን አድርጎ መዋጋት ከጀመረ አንስቶ በሰው ብዛት ከፍተኛ ቁጥር ያሰለፈበት ጦርነት ነው የከፈተው። በሰው ጎርፍ ድል ለማድረግ ቆርጦ ተነስቷል። እናቶች፣ አባቶች፣ ህጻናት፣ በባዶ እጃቸው በሲኖ ትራክ ተሽከርካሪዎች ተጭነው በየግንባሩ ተራግፈዋል። የጦርነቱን ባህሪ ከእስከአሁኑ አካሄዱ በተለየ መልኩ የህዝብ እልቂት የሚፈጸምበት እንዲሆን በማድረግ አቀጣጥሎታል። በአንዳንድ ግንባሮች እስከ 2መቶ ሺህ የሚሆን አብዛኞቹ መሳሪያ ያልታጠቁ እናቶች፣ አባቶችና ህጻናት የተካተቱበት ሃይል አሰልፏል። የመጣው ይምጣ፣ ዘንድሮ ይለይለት ብሎ ለከፍተኛ ዕልቂት ወገቡን አስሮ የጦርነት ነጋሪት ጎስሟል።

እንደጠበቅነው አልሆነም እንጂ ህወሀት ክፉኛ እየተመታ ነው። በየግንባሩ ዕልቂት እያስተናገደ ነው። ትምህርት ቤቶች፣ መስሪያ ቤቶች፣ ፋብሪካዎች ተዘግተው ተማሪውና ሰራተኛው እንዳለ በተሰለፉበት ጦርነት እየሆነ ያለው ለትግራይ ህዝብ አንገት የሚያስደፋ፣ እንደ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሁኔታ ደግሞ ታሪካችን ላይ የማይሽር ጠባሳ የሚተው ነገር ነው እየሆነ ያለው። በእርግጥ የጠበቅነው እንዳይሆን ያደረገው ህወሓት ከ12 እስከ 65 ዓመት ያሉ የትግራይ ተወላጆችን አንድም ሳያስቀር አስገብቶ በማሰለፍ የጦርነቱን ስትራቴጂ በዕልቂት ላይ የሚከናወን እንዲሆን አድርጎታል። እንዲህም ሆኖ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት፣ እንዳሰበው እንዳይገሰግስ ሆኗል። በሙት፣ ቁስለኛና ምርኮ ቁጥር ከኢትዮጵያ ሃይሎች አንጻር የህወሀት ኪሳራ የትየለሌ ነው። ሰሞኑን በጭፍራ እስከ ውርጌሳ ባለው መስመር በተደረገው ጦርነት ያለቀው የህወሀት ጀሌ ቁጥር ስፍር የለውም። በትላንትናው ዕለት 15 ተሳቢ ያላቸው ከባድ ተሽከርካሪዎች ጀሌዎችን ጭነው ተከታትለው ሲጓዙ በድሮን ተመተው እንዳልነበሩ ሆነው መጋየታቸውን ሰምተናል። መሰል ከፍተኛ ጥቃቶች ሰሞኑን በየቦታው ተፈጽመዋል። በመቀሌና አንዳንድ ቦታዎች የሚገኙ ወታደራዊ ተቋማት በአየር ሃይላችን እየወደሙ ናቸው። በአጭሩ ህወሀት እየተቀጠቀጠ ነው። ሆኖም ፕሮፖጋንዳውና የህዝባችን መረበሽ የመከላከያ ሰራዊታችንን ድሎች እንዳይጎሉ አድርጓቸዋል።

በእርግጥ ምርጫ የለንም። መንግስት ላይ ጣት በመቀሰር ህወሀትን ማጥፋት አይቻልም። መንግስት ሀገር የመከላከልና የህዝብን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ ሃላፊነት አለው ማለት ህዝብ እጁን አጣጥፎ ይቀመጣል ማለት አይደለም። ህወሀት በሰነዱ ላይ እንዳስቀመጠው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን መንግስት ማስወገድ የመጨረሻ ግቡ አይደለም። ኢትዮጵያን በኮንፌዴሬሽን መዋቅር በማደራጀትና በመሸንሸን በሂደት ሀገር ማፈራረስ እንደሆነ በግልጽ አስቀምጧል። ህወሀት ዋና ጸቡ ከመንግስት ጋር አይደለም- ከኢትዮጵያና ከህዝቧ እንጂ። ኢትዮጵያን በማዳከም፣ ትንንሽ የጎሳ መንግስታት የሀገር ህልውና ኖሮአቸው እንዲፈጠሩ ማድረግ ነው። ጸቡ ከኢትዮጵያ ጋር ነው። ቂም ይዞ ለማጥፋት ጦርነት ያወጀው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ነው።

ለወሬ የሰጠነውን ቦታ ቀንሰን የህወሀትን እድሜ ለማሳጠር የተጀመረውን ትግል በቻልነው አቅም እናግዝ። መንግስት የሀገርንና የህዝብን ሰላምና ደህንነት ከማስጠበቅ ሃላፊነቱ ለምን ቸል አለ? የህወሀትን ሩጫ ማስቆም ያልቻለው ለምንድን ነው? የሚለው የህዝብ ጥያቄ ተገቢነት ያለው ቢሆንም ሁሉንም ነገር መንግስት ይወጣው ብሎ ማኩረፉና ጣት መቀሰሩ መፍትሄ አይሆንም። የሚወራው ሁሉ እውነት አይደለም። ቢሆን እንኳን መፍትሄው ላይ እንደ ህዝብ ማድረግ ስለሚገባን በአንድ ልብ መወያየት እንጂ በፕሮፖጋንዳው ተሸንፎ ሀገርን አደጋ ውስጥ እንድትገባ በተዘዋዋሪ መርዳት የሚጎዳው እኛኑ ነው። ህወሀት አይደለም ሀይቅን መያዝ ይቅርና አዲስ አበባ አፋፍ ቢጠጋ እንኳን ምን ማድረግ ይገባናል የሚለውን ከስነልቦና ዝግጅት አንስቶ መወያየትና ሀገርን ለማዳን ቆርጦ መነሳት እንጂ በወሬና አሉባልታ ተሸንፎ መቆዘምና ማማረር መፍትሄ አይሆንም።

እንቁረጥ። እንወስን። መንግስት ሃላፊነቱን እንዲወጣ እየወተወትን የህወሀትን ሩጫ በማስቆሙ ሀገር አድን ዘመቻ ፊት መሪ እንሁን። ህወሀት ተስፋ የቆረጠ ቡድን ነው። ጦርነቱ ወዴት እንደሚወስደው የማያውቅ፣ በደመነፍስ የሚንከላወስ ሃይል ነው። የሰው ህይወት መቀጠፉና ንብረት መውደሙ እንጂ በዚህ ጦርነት ህወሀት አሸናፊ እንደማይሆን ያውቀዋል። የአጥፍቶ መጥፋት ሴጣናዊ መንፈስ የሚያሰቃየው መሆኑን ዓለም ተረድቶታል። ይህ ዓይነት እኩይ ሃይል በቀላሉ ይጠፋል ማለት አይቻልም። እየተሽሎከለከ መድፍ በመተኮስ ህዝብን እያሸበረ ህይወት እንዳለው፣ መንግስትን መገዳደር የሚያስችል አቅም መፍጠሩን ለማሳየት የሚያደርገውን የእብደትና የድንቁርና ጦርነት በአሸናፊነት የምንወጣው በቆራጥነትና ልበ ሙሉነት ላይ ስነልቦናችንን አጠናክረን ስንነሳ እንጂ በሆነውም ባልሆነውም ወሬና አሉባልታ ተሸብረን፣ መንግስትን እየተራገምን መሆን የለበትም።

የጊዜ ጉዳይ እንጂ ህወሀት ይጠፋል። ራሳቸው እንዳሉትም ይህኛው ዙር ጦርነት የመጨረሻው ይሆናል። የቁም ኑዛዜ የሚመስለው የእነ ታደሰ ወረደ የቅርብ ጊዜ መግለጫ እውነት ሆኖ የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። የፌንጣ ቁጣ እግሯን እስክታጣ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል።

ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

ለፈጣን ና ታማኝ መረጃዎች ይቀላቀሉን

Photos from Ethio culture business center's post 19/08/2021

Bihaviours of our child shaped by my self

19/08/2021
11/07/2021

We buelding the water dam but not the dimamit

30/06/2021

ኢትዮጲያ የጀግኖች ሐገር ነበረች;አሁንም;ወደፊትም ትቀጥላለች። ጀግኖች አሁንም አሉ ያዉም ጦር ሳዪሆን ኒኩለር የታጠቁ ናቸዉ።

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Gelemso?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Street
Gelemso